የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ተጨማሪ የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት የሽኝት መርሐ ግብር እያካሄደ ነው

By Meseret Awoke

July 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ተጨማሪ የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት የሽኝት መርሐ ግብር በሀዋሳ እያካሄደ ይገኛል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሀገሪቱ እያካሄደ ያለውን የሽብር ተግባር ለመከላከል የደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ማሰማራቱ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ ክልሉ ለሁለተኛ ዙር ነው የልዩ ሀይል አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት በሀዋሳ የሽኝት መርሐ ግብር እያካሄደ ያለው።

ከቆይታ በኋላ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የሽኝት ፕሮግራሙ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!