የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሀት በውጊያ ያስጨረሳቸውን ህጻናት መነገጃ እያደረገ ነው – መከላከያ ሚኒስቴር

By Meseret Awoke

July 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሃት በውጊያ ያስጨረሳቸውን ህጻናት ሬሳ በማሰባሰብ ‘የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊት ገደላቸው’ ብሎ መነገጃ ለማድረግ የተለመደውን የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ለማሰራጨት እየተውተረተረ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አሸባሪው ህወሀት በህጻናት ህይወት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተውተረተረ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል ፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት በአፋር ክልል አለሌ ሱልላ ፣ በአማራ ክልል በቆቦ ከተማ ግራ እና ቀኝ ለትንኮሳ የመጣው የሽብርተኛውን ጁንታ ሀይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ይታወቃል ፡፡

ጁንታው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናትን እያስገደደ እና ከሶስት ቀናት ያልበለጠ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ውጊያ አስገብቶ መቋቋም በማይችሉት ጦርነት እየማገዳቸው ነው ብሏል፡፡

በጦር ሜዳ ባሰለፋቸው ህጻናት ድል አገኛለሁ ብሎ በማሰብ እያስጨፈጨፋቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ይህ ሳይበቃው በውጊያ የተገደሉትን ህጻናት ሬሳ በማሰባሰብ ‘የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊት ገደላቸው’ ብሎ በውጊያ ያስጨረሳቸውን ህጻናት ሬሳ መነገጃ ለማድረግ የተለመደውን የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ለማሰራጨት ሬሳቸውን ኲሐ ላይ ሰብስቦ ይገኛልም ነው የተባለው ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወስኖ ከትግራይ መውጣቱን ካሳወቀ በኋላ የጁንታው ሀይል ሠራዊታችንን ተከትሎ እየተነኮሰ እሱ በፈጠረው ውጊያ የተመታ ሀይል እንጂ ሠራዊታችን የራሱን የማጥቃት ርምጃ እንዳልወሰደ የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!