የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል በአንድ ጀምበር ከ80 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ታቅዷል

By Melaku Gedif

July 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የፊታችን ሃምሌ 20 ቀን በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ80 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱ ተገልጿል፡፡

የክልሉ የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ ሳሙኤል ቀቀቦ ÷ ለችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ  የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በዕለቱም 80 ሚሊየን 300 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ነው የገለፁት።

ለመርሃ ግብሩ ከ30 ሺህ 792  ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ላይ የሚያስፈልጉ ጉድጓዶች ተቆፍረው መዘጋጀታቸውን ጠየቁመዋል።

በተከላ መርሃ ግብሩ  5 ነጥብ 5 ሚሊየን የክልሉ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የችግኝ ተካላ መርሃ ግብሩ በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሚከናወን ሲሆን÷ በዝናብ እጥረት ምክንያት በኮንሶ ዞንና ቡርጂ ተከላው አይካሄድም።

በደቡብ ክልል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ 1  ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የባለሥልጣኑ ዋና ዳሬክተር ከቶ ሳሙኤል ቀቀቦ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከልሉ ለኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ለመስጠት መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በቢቂላ ቱፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!