አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ታታሪ” የተሰኘ የብድርና ቁጠባ ፕሮግራም ለኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች በሃዋሳ ይፋ ተደርጓል፡፡
በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የብድርና ቁጠባ ፕሮግራሙ በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ብሪጅስ ፕሮግራም ነው ይፋ የተደረገው፡፡
ፕሮግራሙም የሰራተኞችን ምርታማነት ለማሳካት ያለመ እንደሆነ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!