አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የመከላከያ ሰራዊት ከአምባ በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በጋራ በመሆን የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናወነ።
የአምባ በጎ አድራጎት ማህበር ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች ለማስመረቅ ለሠራዊታችንን ባደረገው ጥሪ መሠረት ከ40 ህጻናት ተመራቂ ተማሪዎች ጋር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናውኗል።
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ካሌብ ፀጋየ ÷ማህበሩ የሰራዊቱን ልጆች እና የሚንከባከብ ወላጅ የሌላቸውን ህፃናት በመሰብሰብ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል።
ማህበሩን የመሰረቱት የቀድሞ ሰራዊት ልጆች መሆናቸውን ገልፀው ÷ ቀጣይም ለሀገር አንድነት እና ሉዓላዊነት መስዋዕት የሆኑ የሰራዊት ልጆችን በመሰብሰብ ለማስተማር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የሚዲያ እና ፕሮሞሽን ዴስክ አስተባባሪ ሻለቃ ለሜሳ ጎንፋ ፣ ማህበሩ የጀግናው ሰራዊታችንን ልጆች እያገዘ በመሆኑ ከጎኑ ልንቆም ግድ ይለናል ብለዋል።
የአዲስ አበበባ ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ ለማህበሩ መመስረት እና መቆም ለአበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
እርሳቸውም በመልእክታቸው ለሀገሩ ፍቅር እና ለሰንደቁ ክብር ሲል ራሱን አሳልፎ በሚሰጠው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደስተኛ መሆናቸውን እና ማህበሩ ለነገ የሀገር ተስፋ የሚሆኑ ህፅናትን እየከተኮተ በማሳደጉ ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!