የሀገር ውስጥ ዜና

አራት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ET-AMl መለስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ኮምቦልቻ ወረዳ ወደቀ

By Tibebu Kebede

July 27, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት ሰዎችን አሳፍሮ ከድሬድዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረ ET-AMl መለስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ዛሬ ወደቀ፡፡

በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በህይወት መትረፋቸውም ታውቋል፡፡

አውሮፕላኑ ዛሬ ከቀኑ 11:30 አካባቢ በኮምቦልቻ ወረዳ ቄረንሳ ጋረአሮ በተባለ ቦታ መውደቁን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ ተናግረዋል፡፡

ከተሳፋሪዎች መካከል በአንደኛው ተጓዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ድሬደዋ ለህክምና መላኩንም መግለጻቸውን ባልደረባችን ተሾመ ሀይሉ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮን ጠቅሶ ዝግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!