የሀገር ውስጥ ዜና

አሜሪካ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት እንዲያቆሙ አሳሰበች

By Tibebu Kebede

July 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ እያደረሱ ያለውን ጥቃት እንዲያቆሙ የአሜሪካ መንግስት አሳስቧል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የህወሓት ታጣቂ ሃይሎች በትግራይ ስድተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው ተጨባጭ ማስረጃ እንዳሉት አስታውቋል።

መግለጫው በክልሉ በሚገኙ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች፣ በተፈናቀሉ ሰዎች እና የሰብአዊ ድጋፍ ሰራተኞች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት እንዲያቆሙም ጠይቋል፡፡

በኤርትራ ስደተኞች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የመጀመሪያ አለመሆኑን ያነሳው መግለጫው ከዚህ ቀደም ባለፈው ጥር ወር ተመሳሳይ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተጨባጭ ማስረጃዎች እንዳሉትም ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!