የሀገር ውስጥ ዜና

ለ1 ሚሊየን 620 ሺህ 180 የመለኪያ መሳሪያዎች የትክክለኛነት ማረጋገጫ ተሰጠ

By Meseret Awoke

July 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የሸማቹንና የነጋዴውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለ1ሚሊየን 620 ሺህ180 የመለኪያ መሳሪያዎች የህጋዊ ስነ ልክ መስፈርቶችን ትክክለኛነት ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ፈቃድ ሰጠ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትክክለኛነት ልኬት ካደረገባቸው የተለያዩ የልኬት ቁሳቁሶች መካከል ልዩ ልዩ ሚዛኖችና የክብደት ማነፃጸሪያዎች፣ የምድር ሚዛኖች፣ የርዝመት መለኪያዎች እና የፈሳሽ መለኪያዎች ይገኙበታል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለፈሳሽ ማጓጓዣ ቦቴዎችም ልኬት አድርጎ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

የህጋዊ ስነ-ልክ ዳይሬክተር አቶ ያሬድ በፍቃዱ የአውቶ ቦቴ ቬሪፊኬሽን ማዕከልን ለማዘመን የሚያስችሉ ጥናቶች ተካሂደዋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!