አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 የአረንጓዴ አሻራ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ማደስና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በድሬ ዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የምስራቅ ኢትዮጰያዋ የንግድና ኢንዱስትሪ ከተማዋ ድሬደዋ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች የ2013 የአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፈቃድ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ማደስና የፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተመራጭ ከተማ ሆናለች።
የከተማው መስተዳደር አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች በጎአድራጊ ተቋማትና የወጣት አደረጃጀቶች በዚህ ተምሳሌታዊ በጎ ተግባር እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!