የሀገር ውስጥ ዜና

ሃገራዊ ጥሪውን የተቀበሉ የቤንች ሸኮ ዞን ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው

By Tibebu Kebede

July 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቤንች ሸኮ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች ሃገር የማዳን ተልዕኮን ለመወጣት መከላካያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

ወጣቶቹ ለእናት ሀገራቸው ለመታገል እድሉን በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን እና ማንኛውንም መስዋዕትነት ለሀገር ክብር ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ወጣቶቹ አክለውም አሸባሪው የህወሓት ቡድን እንዲጠፋ ሌሎች ወጣቶችም ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መላው የኢትዮጵያ ህዝብም አንድነቱን አስጠብቆ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲቆምም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በፍሬው አለማየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!