አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይደናገጥ የአካባቢውን ሠላምና ደህንነት ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ደህንነት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሐሰን መሃመድ እንደገለጹት የህወሓት ጁንታ በደሴ ከተማ ገባ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የተለመደ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡
መላው የደሴ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብም የህወሓት ጁንታ በሚያስተላልፈው የአሉባልታ ወሬ ሳይደናገጥ የአካባቢውን ሠላምና ደህንነት ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ተደራጅቶ መጠበቅ ይገባዋል ብለዋል፡፡
የጁንታውን ሃገር የማፍረስ ሴራ በመመከት በቀጠናው አስተማማኝ ሠላምና ደህንነት እንዲሰፍን ከአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ጋርም በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከደሴ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች፣ ማህበራት፣ እድሮች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የከተማዋን የመውጫና የመግቢያ በሮችን በተጨማሪም የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ላይም የተናጠከረ ልዩ ፍተሻና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በይከበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!