የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስትሯ ከተመድ የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

July 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት መንግስታት የፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በውይይቱ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ከአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ አስመልክቶ በስፋት መክረዋል።