አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ምቹ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጊያ itsmydam.et በሚል አዲስ ዌብሳይትና የሞባይል መተግበሪያ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀመረ።
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፣ የኢትዮጵያ የሰላምና የእርቅ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ድጋፍ ለአባይ አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካዮች እና ሌሎች እንግዶች ከአውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ በተገኙበት የምረቃው ስነ-ስርአት በበይነ መረብ ተካሂዷል።
ድረ ገጽን መሠረት ያደረገ የገንዘብ ማስተላለፊያ ሶፍትዌሩ የበለጸገው ቻፓ ሶሊዩሽን ኮርፖሬሽን በተባለ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ተቋም ሲሆን የሞባይል መተግበሪው ደግሞ በለንደን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!