አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የወረዳ ህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡