የሀገር ውስጥ ዜና

የሱዳን ምሁራን የልዑካን ቡድን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

By Meseret Awoke

August 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ምሁራን የልዑካን ቡድን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ወቅታዊ ችግር ለመፍታትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ከጥንት ጀምሮ ያላቸውን ታሪካዊ የባህል ትስስር የሚገልፁ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በሱዳን ፕሮፌሰሮች መቅረባቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሃገራቱን ምሁራን በማስተሳሰርና በማስተባበር ከአባይ /ከታላቁ የህዳሴ ግድብ/ ጋር ተያይዞ የምርምር ተቋማትን በኢትዮጵያና በሱዳን በመመስረት የጋራ ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ በመድረኩ ተገኝተው አብራርተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!