የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር ትህነግን ለመደምሰስ አገልግሎት የሚውል ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

August 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ጠበቆች ማኅበር አባላት አሸባሪው ትህነግን ለመደምሰስ አገልግሎት የሚውል ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የማኅበሩ አባላት ከባሕር ዳርና አካባቢዋ ጠበቆች ጋር ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አባላቱ ለህልውና ማስከበሩ ለዘመቱት ኀይሎች ገንዘብ እያሰባሰቡ እንደሚገኙና ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከሚኖሩ ጠበቆች 1ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅደው እስካሁን 100ሺህ ብር መሰብሰባቸውን ነው የተናገሩት፡፡ አባላቱ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች የገንዘብ ድጋፍ እያሰባሰቡ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!