የሀገር ውስጥ ዜና

የገዳ ባንክ አክሲዮን ማህበር የምሰረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገዳ ባንክ አክሲዮን ማህበር የምሰረታ ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የባንኩ የቁጠባ ባህልን ለማሻሻልና በገጠር የሚኖረውን ማህበረሰብ ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

በምስረታ ጉባኤው የባንኩ ቦርድ አባላት ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!