የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው የ37 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል ፕሮጀክቶችን ማስመዝገቡ ተገለፀ

By Meseret Awoke

August 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዳያስፖራው የ37 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል ፕሮጀክቶችን ማስመዝገቡን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ።

ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት 3ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 84 ፕሮጀክቶች ስራ መጀመራቸውን አስታውቀው÷ በተጠናቀቀው በጀት አመት 37 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያላቸው 1ሺህ 992 የንግድና 1ሺህ 994 የኢንቨስትመንት የዲያስፖራ ፕሮጀክቶች ተመዝግበዋል።

ከነዚህ ውስጥ 3ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 84 ፕሮጀክቶች በአዲስ አበባ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች ወደ ስራ መግባታቸውን አስታውቀው÷ ፕሮጀክቶቹ ለ13 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል።

እንደ ኢፕድ ዘገባ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ የሀገር ውስጥ አካውንት የሚከፍቱ የዲያስፖራ አባላት ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

በ2013 የበጀት አመት ወደ 8ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ተቀማጭ የሆነበት በርካታ የዳያስፖራ አካውንቶች መከፈታቸውንም ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!