የሀገር ውስጥ ዜና

በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ መሰረታዊ ሸቀጦች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ተደርገዋል

By Feven Bishaw

August 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ክልሎች በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ መሰረታዊ ሸቀጦች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ መደረጉን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የዋጋ ውድነቱን ለመፍታት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ እንደገለፀው÷ መንግስት በድጎማ የሚያቀርባቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ከራሱ ምንጭ የውጭ ምንዛሬ በመመደብና የውጭ ምንዛሬ ባላቸው ባለሃብቶች ከታክስና ከግብር ነጻ ሆኖ ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ ይገኛል።