አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጄሪያ ጦር በአየር ጥቃት 78 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ።
የሃገሪቱ አየር ሃይል እንዳስታወቀው አብዛኞቹ ታጣቂዎች በተሽከርካሪ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የናይጄሪያ የፀጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
ከፈረንጆቹ ታህሳስ ወር ጀምሮ ታጣቂዎቹ ከ 1 ሺህ በላይ የትምህርት ቤት እና የኮሌጅ ተማሪዎችን እንዳገቱ ይታወሳል፡፡
ከዚህ ውስጥ 300 ያህሉ ህፃናት ተማሪዎች አሁንም በእገታ ላይ እንደሚገኙ ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡
የሃገሪቱ ባለስልጣናት የታጣቂዎችን እርምጃ አላስቆሙም በሚል ወቀሳ ይቀርብባቸዋል።