የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሐፈት ቤት ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ወሰኑ

By Feven Bishaw

August 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሐፈት ቤት ሠራተኞች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸው ተገለፀ፡፡

ሰራተኞቹ ለቀረበው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠትና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ ነው የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት የወሰኑት፡፡