የሀገር ውስጥ ዜና

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ በብሄራዊ ቴአትር እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

August 06, 2021

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዩ ኢትዮጵያዊነት ይሞታል ሲሉት የማይሞት፣ ይደቃል ሲሉት የማይከስም አበቃለት ሲሉት የሚለመልም ነው ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ፈተና እድል ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ ፈተናዎች ሀገራዊ አንድነትን ይጨምራሉ፣ ይሰበስባሉም ያሉ ሲሆን አድዋን በማሳያነት አንስተዋል።

ከፀጋዬ ገብረመድህን እስከ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ከጥላሁን ገሰሰ እስከ መሀሙድ አህመድ ስለኢትዮጵያ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን መስራታቸውን አንስተው ይሄኛው ትውልድም በጥበብ ስራ ታሪክ እንደሚፅፍ ገልፀዋል።

አሸባሪው ህወሃት የጫረውን እሳት ተከትሎ የጥበብ ባለሙያዎች በግንባር እንደሚገኙ አውስተው በተሰማራንበት መስክ ሁሉ ለሀገር አንድነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በአፈወርቅ እያዩ