የሀገር ውስጥ ዜና

የአካል ጉዳተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር በእውቀት የተደገፈ የአካታችነት ስራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

By Feven Bishaw

August 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ጉዳተኞችን አሳማኝና ብቁ የሆነ የፖሊሲ፣ የልማት ዕቅድና ስትራቴጅ፣ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች አካታችነት ላይ ያተኮረ የህግ ባለሙያዎች መድረክ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ምክትል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ፍቃዱ ፀጋ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ያለ አካል ጉዳተኞች ንቁ ተሳትፎና አካታችነት የሀገር ልማትና እድገት አይረጋገጥም።