የሀገር ውስጥ ዜና

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በነገው እለት ያስመርቃል

By Feven Bishaw

August 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ 3 ሺህ በላይ ተማሪዎች በነገው እለት ያስመርቃል፡፡

ዩኒቨርስቲው በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በርቀትና በክረምት መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 388 ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው።