የሀገር ውስጥ ዜና

በነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Feven Bishaw

August 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በነሐሴ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ ያለው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በነሐሴ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ምርት ውጭ ያሉ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን ጠቁሟል።