የሀገር ውስጥ ዜና

የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ተጠባባቂ ሃይሎች በባሕር ዳር ከተማ ምረቃ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ለህልውና ዘመቻው የክተት ጥሪውን ተቀብለው ወደ ስልጠና የገቡ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ ተጠባባቂ ኀይሎች በባሕር ዳር ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ ምረቃ እየተካሄደ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!