የሀገር ውስጥ ዜና

የህወሓት ጁንታን በመቃወምና ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ የነቀምቴ ከተማ እና የምስራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ሰልፍ አካሄዱ

By Meseret Awoke

August 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የህወሓት ጁንታን በመቃወም እና ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ የነቀምቴ ከተማ እና የምስራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በሰልፉ የተገኙት የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን እንደገለጹት÷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለማንም አትሰግድም፤ አትፈርስም ብለዋል፡፡

የምስራቅ ወለጋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ በበኩላቸው÷ የነቀምቴ ከተማ እና የዞኑ ነዋሪዎች ጁንታው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ከወንድሞቹ ኢትዮጵዊያን ጋር በመሆን በአጭር ጊዜ እንዲደመሰስ አሰፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡

አሁን የአሸባሪው ቡድን ርዝራዦች ከጌቶቻቸው በሚያገኙት ድጋፍ ሀገርን ለማፍረስ እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ይህንን እኩይ ተግባር ለማጥፋት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን በሚፈለገው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ድሉ በአጭር ጊዜ እንዲፈጸም ሀላፊነታቻንን መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በሰልፉም የተለያዩ መፈክሮች መደመጡን የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!