የሀገር ውስጥ ዜና

ሽብርተኛው ቡድን በአፋር ህዝብ ላይ የፈጸመው ጥቃን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ ጥሪ ቀረበ

By Meseret Awoke

August 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው የህወሓት ቡድን በአፋር ህዝብ ላይ የፈጸመው ጥቃን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ ጥሪ ቀርቧል።

ሽብርተኛው ቡድን በክልሉ ፋንተሩሲ እና ከልዋንን በመሰሉ ዞኖች አካባቢ በርካታ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በሎጊያ አካባቢ በጊዜያዊነት ተጠልለው ይገኛሉ።

የጁንታው ሃይል በፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት ህይዎታችን እንዲመሰቃቀል ሆኗል ያሉት ተጎጂዎቹ÷ የሽብር ድርጊቱ ልብ ሰባሪ እንደሆነም ገልጸዋል።

ለተጎጂዎቹ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የጋዜጠኞች ቡድን በአካባቢው በነበረው ቅኝት ተመልክቷል።

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኡመር መሃመድ÷ የክልሉን ነዋሪዎች በማስተባበር ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

እስከካሁን ከ6መቶ ሺህ በላይ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ከ1 ሚሊየን በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች በአይነት ከህብረተሰቡ ድጋፍ ተደርጓል።

ተጎጂዎችን ለመደገፍ ከማህበረሰቡ በኩል ያለው ተሳትፎ በመልካም ጎኑ መነሳት ቢችልም÷ ካለው የተጎጂዎች ቁጥር አንጻር ድጋፉ መጠናከር እንደሚገባውም የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ገልጿል።

በሃገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተጎጂዎች ጎን እንዲቆሙም ጥሪ ቀርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!