አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጁት ኦነግ ሸኔ እና ህወሓት ከዚህ በፊ በድብቅ ሲፈጽሙት የነበረውን የጥፋት ተግባር ለማስቀጠል በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
የኦነግ ሸኔ መሪ ድሪባ ኩምሳ (ጃል መሮ ) ከአሶሺየትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ÷መንግስትን በሃይል ከስልጣን ለማውረድ ከህወሓት የሽብር ቡድን ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ የሽብር ቡድኑ ህወሓት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከጥቂት ሳምንታት በፊት መፈጸሙን ነው የገለጹት፡፡
የሽብር ቡድኑ ህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ዶክተር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በበኩላቸው ÷ከኦነግ ሸኔ ጋር በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ በጥምረት ለመስራት ውይይት መጀመራቸውን ለሬውተርስ የዜና ወኪል አረጋግጠዋል፡፡
መንግስት ኦነግ ሼኔ ከህወሓት የሽብር ቡድን የጥፋት ተልዕኮ በመቀበል በተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሲፈጽም መቆየቱን በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወቃል፡፡
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤትም ሁለቱን ቡደኖች በአሸባሪነት መፈረጁ የሚታወስ ነው፡፡
ኦነግ ሸኔ እና ህወሓት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!