አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ከሀምሌ 01 እስከ ሀምሌ 30/2013 ዓ.ም በሶስቱም ደረጃ ግብር ከፋዮች 5 ቢሊየን 820 ሚሊየን 260 ሺህ ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ቢሮው ለመሰብሰብ ካቀደው 5 ቢሊየን 390 ሚሊየን 930 ሺህ ብር የሰበሰበው 5 ቢሊየን 820 ሚሊየን 260 ሺህ ብር ነው፡፡
በዚህም የዕቅዱን 108 በመቶ ማሳካት መቻሉ ነው የተገለፀው፡፡
ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 1 ቢሊየን 126 ሚሊየን 950 ሺህ ብር ወይም 24 በመቶ ብልጫ መኖሩ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!