የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከስፔን ድንበር የለሽ ሀኪሞች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

August 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የስፔን ድንበር የለሽ ሀኪሞች ዳይሬክተር ቴሬሳ ሳንክሪስቶራል ጋር መወያየታቸው ተገለፀ፡፡

ሚኒስትሯ በቅርቡ ህይወታቸውን ባጡት የስፔን ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው÷ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

ክስተቱም በወቅቱ አለም ዓቀፍ ትኩረት ለመሳብ በህወሓት የተፈጸመ መሆኑን መረጃዎች እንደሚያሳዩ አብራርተው÷ በጉዳዩ ላይ ክትትል ሲደረግ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የህክምና ቡድኑ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያከናወነ ያለውን የሰብዓዊ ተግባራት የሀገሪቱን ህግና ደንብ እስካከበሩ ድረስ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መወያየታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!