የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገራችንን ለማዳን እንዘምታለን -የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች

By Meseret Demissu

August 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች ሀገራችንን ለማዳን እንዘምታለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ሠራተኞቹ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ እና ሀገር ላይ የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።

በሀገር ላይ የተቃጣውን ወረራ ለመመከት ሁሉም ዜጋ “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ የትም፣ መቼም፣ በምንም” በሚል መሪ ቃል ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞችም ይህንኑ እውን ለማድረግ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ድጋፍ ለማዋል፣ ደም ለመለገስ እና ስንቅ ለማዘጋጀት  ተስማምተዋል።

ከሠራተኞቹ መካከልም ሀገራችን ስትወረር ተቀምጠን አናይም በማለት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ቃል መግባታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!