የሀገር ውስጥ ዜና

ከመዲናዋ የተውጣጡ 45 የህክምና ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው

By Meseret Demissu

August 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ሆስፒታሎች የተውጣጡ 45 የህክምና ባለሙያዎች በኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገኝተው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የህክምና ቁሶችን አሟልቶ ወደ ቦታው ያመራው የህክምና ቡድኑ ፥በባለሙያ እጥረት አልያም በመድሃኒት ችግር የአንድም ጀግናው ወታደር ሕይወት እንዳታልፍ በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ  ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!