አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝቡ አሸባሪው ትህነግን እሾህ ሆኖ እየወጋውእንደሚገኝ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ገለጹ፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለም ወርቅ አሸባሪው ትህነግ ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች የእምነት ቦታዎችን፣ ተቋማትን እና የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን እንዳወደመ ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ንጹሓን ዜጎችን ገሏል፣ የግለሰብም ሆነ የመንግሥት ንብረቶችን ባደራጀው ቡድን ዘርፏል ብለዋል፡፡
በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በጋይንት አካባቢ ለመግባት የሞከረው አሸባሪው ቡድን በሀገር መከላከያ፣ በልዩ ኃይል፣ በሚሊሻ እና በፋኖ ጥምረት እየተደመሰሰ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
ነዋሪው ሕዝብም እሾህ ሆኖ እየወጋው ይገኛል ብለዋል፡፡
ሌሎች አካባቢዎችም እንደ ጋይንት እና አካባቢው ሕዝብ አሸባሪውን ትህነግ የደረሰበት ሁሉ መውጫ መግቢያ በማሳጣት መደምሰስ እንዳለበት ማሳሰባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!