የሀገር ውስጥ ዜና

ተተኳሽ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

August 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምቦ ከተማ 1 ሺህ 377 ተተኳሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ የተገኙ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ ጥይቶቹን የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 4-28212 ኢት በሆነ አምቡላንስ ተሽከርካሪ ጭነው ሲያጓጉዙ እንደተገኙ የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሲሳይ ሂርጳ ገልጸዋል።