የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በወሎ ግንባር በመገኘት በስፍራው የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አበረታቱ

By Feven Bishaw

August 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በወሎ ግንባር በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት በአካል ተገኝተው አበረታትተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አገሪቷ የገጠሟትን ፈተናዎች ፊት ለፊት በመፋለም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለ ያለ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን ገልጸዋል።