የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ወሎ ዞን የዘማች አርሶአደሮች ሰብል እየታረመ ነው

By Feven Bishaw

August 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን የዘማች አርሶአደሮች ሰብል እየታረመ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ዞኑ ደሴ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች የሀገርን ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ ግንባር ድረስ የተጓዙ ቤተሰቦችን ሰብል እየተንከባከቡ ይገኛሉ።