የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረሪ ክልል በ16 ሚሊየን ብር የተገነቡ የትምህርት መሠረተ ልማቶች ተመረቁ

By Meseret Awoke

August 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል በ16 ሚሊየን ብር የተገነቡ የትምህርት መሠረተ ልማቶች ተመርቀዋል፡፡

በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦድሪን በድሪ የተመራ የልዑክ ቡድን በክልሉ ኤረር ወረዳ የተገነቡትን ሁለት ትምህርት ቤቶች መርቆ ስራ አስጀምሯል።

በህዝቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሠረት ትምህርት ቤቶቹ መገንባታቸውን የገለፁት የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሚስራ አብደላ÷ ህብረተሰቡ በትምህርት ቤት ጥራት ምክንያት ሲያነሳቸው የቆየውን ቅሬታዎች የሚፈታ ነው ብለዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊ በበኩላቸው÷ የትምህርት ቤቶቹ መገንባት በኮቪድ-19 ምክንያት የተፈጠረውን የክፍል ጥበት እንዲፈቱ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በሐረሪ ክልል በ100 ሚሊየን ብር ሰባት ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙ ተገልጿል።

በምንያህል መለሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!