የሀገር ውስጥ ዜና

የኪነጥበብ ባለሙያዎች በወሎ ግንባር ለሚገኙት የጸጥታ አካላት የጥበብ ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ነው

By Melaku Gedif

August 16, 2021

በመድረኩ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎሉ ቀረርቶዎች፣ ሽለላ እና  ፉክራዎች እንዲሁም  ሙዚቃዎችና ስነ ጽሁፋዊ ስራዎች እየቀረቡ ነው።

በመድረኩ የተገኙ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የጥበብ ስራዎችን ከማቅረብ ባለፈ ለሀገር የሚከፈለውን መስዕዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታውን  ነው ያረጋገጡት ፡፡

ሁሉም ነገር ሊኖር የሚችለው ሀገር ስትኖር በመሆኑ በሀገር ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ሁሉም  የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ጠላት ቀይ መሥመር አልፏል ያሉት ባለሙያዎቹ÷  ወጣቶች መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልን እና  ሌሎች አደረጃጀቶችን በመቀላቀል ሀገራቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል።