የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ምዝገባ እንዳያደርጉ ውሳኔ አሳለፈ

By Feven Bishaw

August 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ትምህርት ቤቶች በወርሃዊ ክፍያ ላይ አላግባብ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ምንም አይነት ምዝገባ እንዳያደርጉ ውሳኔ ማሳለፉን የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአስተዳደሩ ልጆቻቸውን በግል ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ወላጆች በተደጋጋሚ በወርሃዊ ክፍያ ላይ የሚያደረገው ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን ያላገናዘበ ነው ብለዋል።