የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒሴፍ ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ  አደረገ

By Meseret Demissu

August 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአማራ ክልል ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ 9 ሺህ 130 ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድርጅቱ ለተፈናቃዮች የምግብ፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኩል ማድረጉን ገልጿል።

በቀጣይም የህይወት አድን ድጋፉን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባለው የህልውና ዘመቻ በአማራ ክልል 674 ሺህ 492 ተፈናቃዮች እንደሚገኙም ነው ዩኒሴፍ  በትዊተር ገጹ ያስታወቀው ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!