የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ያቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን አመሰገኑ

By Meseret Awoke

August 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም” በሚል መሪ ቃል፣ የብሔራዊ ቴአትር፣ የኦሮሞ የባህል ማዕከልና የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል፡፡

“ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው መልእክታቸውን አስፍረዋል፡፡

በዚህም ዝግጅቶቹን ላቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን÷ “ሌሎችም ከያንያን አርአያነታችሁን እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል፡፡

ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!