አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከብሄራዊ ስታቲክስ ኤጀንሲና አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን አገር አቀፍ የሠው ሃይልና ፍልሰት ላይ ጥናት አካሂደዋል።
በዚህም ጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰው ሀይል የተሳትፎ ምጣኔው ከ100 ለስራ ከደረሱ ሰዎች ውስጥ 65 ሰዎች በምርት ስራ ለመሰማራት ዝግጁ ናቸው ተብሏል።
ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለ ወጣት ህዝብ ያላት ና የታዳጊ ኢኮኖሚ ባለቤት በመሆኗ የሰው ሀይሉን በአግባቡ ለሀገር ጥቅም እንዲውል ለማድረግ ጥናቱ ወሳኝ ነው ተብሏል።
በጥናቱ ወቅታዊ የሰው ሀይል፣ስራ ስምሪት፣ስራ አጥነት፣የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ፍልሰት፣ኮሮናን መከላከልና ያስከተለው ተጽእኖን የሚመለከቱ መረጃዎችን ይዞ ወጥቷል።
በዚህም መረጃ አጠቃላይ የስራ አጥ ምጣኔው ስምንት በመቶ፣የሀገር ውስጥ ፍልሰት 17 ነጥብ 1 በመቶ፣ዓለም አቀፍ ፍልሰት ከስደት ተመላሽ 77 በመቶ ከመካከለኛው ምስራቅ 13 በመቶ ከአፍሪካ ሀገራት መሆኑ ተመላክቷል።
ስለ ኮሮና የቤተሰቦች ግንዛቤ መከላከልና ተጽእኖ 84 በመቶ እጅ መታጠብ፣75 በመቶ ማስክ ማድረግ፣53 በመቶ ርቀትን መጠበቅ፣ 40 በመቶ ሳኒታይዘር በመጠቀም ኮሮናን ለመከላከል ግንዛቤ እንዳላቸው በጥናቱ ተረጋግጧል።
ኃይለየሱስ ስዩም