አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ወሎ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይልና ለሚሊሻ አባላት ግንባር ድረስ በማቅናት ከ780 ሺህ ብር በላይ የሆኑ 24 ሰንጋዎችና 46 በጎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሠይድ መሐመድ በግንባር ተገኝተው÷ በዞኑ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የተሰባሰበውን ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
አሸባሪውና የትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ እየተደረገ ያለውን ጥረት በፍፁም ወኔና ብቃት በመከወን ኢትዮጵያን በጽኑ መሰረት ላይ ለማስቀጠል ሠራዊቱ እያደረገ ያለውን ዝግጅትና ተጋድሎ አድንቀዋል፡፡
በዚህ ሂደት የዞኑ ህዝብ ለሠራዊቱ ከደጀንነት ባለፈ ሁሉን አቀፍ እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱም ከደቡብ ወሎ ዞን ጃማ፣ ወረኢሉ፣ ደሴ ዙሪያና አልብኮ ወረዳዎች ግምታቸው ከ780 ሺህ ብር በላይ የሆኑ 24 ሰንጋዎችና 46 በጎችን የፌዴራል፣ የክልልና የዞን አመራሮች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ለሠራዊቱ አስረክበዋል፡፡
በቀጣይም የህልውና ዘመቻው እስከሚጠናቀቅ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተዳዳሪው መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!