አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሠራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የባንኩ ማኔጅመንት አባላትና መላ ሠራተኞች ዛሬ ባካሄዱት ስብሰባ፥ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
ሠራተኞቹ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ሠጥተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ቀደም ሲል ሲያደርጉት እንደቆዩት ሁሉ ደም መለገሳቸውን እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል።
ሠራተኞቹ ከደጀንነት በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመሄድ ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል።
ባንኩ በላከልን መረጃ ወደ ግንባር ለመዝመት ተመዝግበው ለመሄድ የተዘጋጁ የባንኩ ባልደረቦች መኖራቸውም ታውቋል።
ሠራተኞቹ ለሠራዊቱ በቀጥታ ከሚያደርጉት ድጋፍ ጎን ለጎን በተሠማሩበት የሙያ መስካቸው የበለጠ በመትጋት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!