ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሃይቲ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Alemayehu Geremew

August 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃይቲው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ 1 ሺህ 941 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 2 መለካቱም ነው የተነገረው።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 10 ሺህ የሚጠጉ የሀገሪቷ ዜጎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የተገለፀው፡፡

ከዚህ ባለፈም በርካቶች የደረሱበት እንዳልታወቀ ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።፡

ከአደጋው የተረፉ ዜጎችን ለመታደግ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነብስ አድን ስራ እያነከናወኑ ቢሆንም፥ በወቅቱ የጣለው ከባድ ዝናብ አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩም ነው የተገለፀው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለፀው ደግሞ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ ሕፃናት መጠነኛ ወይም ምንም አይነት የመጠለያ፣ የንፁህ ውሃ እና የምግብ አቅርቦት እያገኙ አይደለም፡፡

በአሁኑ ወቅት የሃይቲ ነዋሪዎች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ምንም አይነት ሐብት፣ ንብረት እንዲሁም መጠለያ እንደሌላቸውና ውሃ ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ ዩኒሴፍ ገልጿል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!