የሀገር ውስጥ ዜና

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

August 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ከ1ነጥብ1 ሚሊየን ብር በላይ ሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሸባሪው የህውሓት የጥፋት ቡድን በመንግስት የተሰጠውን የሰላም እድል ወደ ጎን በመተው ሃገር የማፍረስ አጀንዳውን በመቀጠሉ መንግስት እያካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ ተጋድሎ ለሚያደርገው የመከላከያ ሰራዊት ነው ድጋፍ ያደረጉት።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን፣ የኤምባሲው ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣ማሪታይምና ትራንዚት አገልግሎት ሠራተኞች ፣በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ፣በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፣ በጅቡቲ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በጅቡቲ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የህልውና ዘመቻ እያደረገ ያለውን የመከላከያ ሰራዊትን በሚያደርገው ተጋድሎ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንደሚሰለፉ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!