አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የጤና መድህን ኤጀንሲ ሰራተኞች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚውል ከ1 ሚሊየን 651 ሺህ በላይ ብር አሰባሰቡ፡፡
በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉ ሠራተኞች ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ከደመወዛቸው ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚውል ቃል ገብተዋል፡፡
ድጋፉን በተመለከተ የተቋሙ አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሀገሪቱን ለማዳንና ለማሻገር በሚደረገው ትግል ውስጥ ሁሉም የበኩሉን እየተወጣ በመሆኑ የሚበረታታና የሚደነቅ ተግባር ስለሆነ ለተቋሙ ሰራተኞች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም የተቋሙ ሰራተኞች መደበኛ የልማት ስራዎች ዕቅድ ለማሳካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መትጋት ይጠበቅባቸዋናል ማለታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!