የሀገር ውስጥ ዜና

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ደም ለገሱ

By Meseret Awoke

August 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ ተቋማት ከሆኑት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች ጋር ዛሬ ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል፡፡

የደም ልገሳ መርሐ ግብሩ÷ ‹‹ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን›› በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው ንቅናቄ አካል ነው ተብሏል፡፡

በመርሃ ግብሩ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የደም ልገሳ ማድረጋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በደም ልገሳው ወቅት የተገኙት አመራሮች እና ሠራተኞች ውዱን እና በገንዘብ የማይተመነውን ደም ለመከላከያ ሰራዊት በመለገሳቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው የገለጹ ሲሆን÷ የህግ ማስከበር ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡

በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት የትኛውንም ነገር የማድረግ ሀላፊነት አለብን ያሉት አመራር እና ሠራተኞቹ÷ መስዋዕትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውንም ነው የገለፁት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!