አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ጥቃት የደረሰባቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ ከ 20 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡
የሰመራ ከተማ ከንቲባ አሊ መሃመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷የተጠቀሰው ገንዘብ መጠን ቃል የተገባውንም ይጨምራል፡፡
ድጋፉ በገንዘብ እና በአይነት የተደረገ ሲሆን ÷ የተገኘውም ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ከሚኖሩ የክልሉ ነዋሪዎች እና ተወላጆች መሆኑን ጠቁመዋል።
ከድጋፉ በተጨማሪ የከተሞቹን ሰላም ዘላቂ ለማረጋገጥ ከነዋሪዎች ጋር በመወያየት የከተሞቹን ሰላም ለማስቀጠል በምሽት ጭምር በፈረቃ አካባቢያቸውን የመጠበቅ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በጁንታው የሀሰት ወሬዎች ህዝቡ እንዳይታለልም ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየሰሩ መሆኑን ዋና ከንቲባው ተናግረዋል።
አሁን ላይ ጁንታው የአፋርን ወጣት እንደ ቀድሞው ማታለል እንደማይችልም ነው የተገለፀው፡፡ በጥበበስላሴ ጀምበሩ እና አወል አበራ
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!